በኢትዮጵያ ሁለተኛው የቴሌኮም አገልግሎት ሰጪ ኩባንያ የሆነው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸሙን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ እንደ መግለጫው ከሆነ የሳፋሪኮም ቴሌኮም አገልግሎቶች ለ46 በመቶ ኢትዮጵያዊያን የተዳረሰ ሲሆን የኔትወርክ ሳይቶች ብዛት ደግሞ ወደ ሶስት ሺህ ከፍ ብሏል፡፡ ...